የቫንኮቨር ንዑስ ማእከል በገዳመ ቅዱሳን ሐዊረ ሕይወት አካሄደ፡፡

የቫንኮቨር ንዑስ ማእከል በገዳመ ቅዱሳን ሐዊረ ሕይወት አካሄደ፡፡

<><><>+<><><><>+<><><>+<><><>+<><>

የቫንኮቨር ንዑስ ማእከል በገዳመ ቅዱሳን (All saints orthodox Monastery) ሐዊረ ሕይወት አካሄደ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በካናዳ ማእከል የቫንኮቨር ንዑስ ማእከል በገዳመ ቅዱሳን (All saints orthodox Monastery) የሐዊረ ሕይወት/የሕይወት ጉዞ/ መርሐ ግብር አካሄደ ፡፡ በዕለቱ ከ180 ምዕመናን በላይ በጉዞው ተሳትፈዋል፡፡

በሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብሩ ዝማሬ፣ ትምህርተ ወንጌል፣ምክረ አበው፣ እንዲሁም በመርሐ ግብሩ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮችም ተዳስሰውበታል፤በተሳታፊዎች መንፈሳዊ ውይይት ተከናውኗል፤ ስለጉዞው ስለመርሐ ግብራቱና ስለ ዝግጅቱ ምእመናን ሐሳብ እንደሰጡት የሕይወት ጉዞው በመንፈሳዊነት ለማደግና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለመትጋት ስንቅ እንደሚሆናቸው አስተያየት ሰጥተዋል፤መርሐ ግብሩን ለአዘጋጁት አስተባባሪዎችም ምስጋና አቅርበው ይኸ ዓይነት ጉዞ ከሌሎች ንዑሳን ማእከላትም ጋር በመሆን ቢቀጥል የሚሉና ሌሎችም ገንቢ አስተያየት ተሰጥቶ የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል፡፡ ተጓዦችም በእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ወደ መጡበት ቦታ በሰላም ተመልሰዋል፡፡