• እንኳን በደኅና መጡ !

“ኢየሱስም ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ተጠመቀ፡፡” ማር 1÷9

“ኢየሱስም ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ተጠመቀ፡፡” ማር 1÷9 ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድሰት ድንግል ማርያም በኅቱም ድንግልና ተጸንሶ በኅቱም ድንግልና ተወልዶ በተወለደ 40 ቀኑ ዕጉለ ርግብ ዘውገ ማዕነቅ ይዞ ወደ ቤተ መቅደስ በመግባት፣በዓመት ሦስት ጊዜ ለበዓል ኢየሩሳሌም በመውጣት ሕግ መጽሐፋዊን ሕግ ጠባያዊን እየፈጸመ “በበህቅ ልህቀ እንዘ ይትኤዘዝ ለአዝመድሁ እንተ […]

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን የመላእክት አለቃ የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። እርሱም በባቢሎን አገር ከነደደ እሳት ውስጥ በጨመሯቸው ጊዜ አናንያን አዛርያን ሚሳኤልን ያዳናቸው ነው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአማልጅነቱ ይማረን ለዘለዓለሙ አሜን። አርኬሰላም ዕብል ኪያከ ክቡረ፤ለስመ ዚአከ […]

“መላእክት ዘወትር ምግብሽን እያመጡ፤በቤተ መቅደስ ኖርሽ” አንቀጸ ብርሃን

“መላእክት ዘወትር ምግብሽን እያመጡ፤በቤተ መቅደስ ኖርሽ” አንቀጸ ብርሃን የእመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ መግባት ኢያቄምና ሐና የሚባሉ በተቀደሰ ትዳር የሚኖሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ልጅ አልነበራቸውም ፤ ሐናና ኢያቄም ልጅ ስለሌላቸው ያዝኑ ነበር፤ሁልጊዜም ወደ ቤተ እግዚአብሔር እየሄዱ እግዚአብሔር ልጅ እንዲሰጣቸው ልመና ያቀርቡ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሲሄዱ ሐና “ርግቦች ከልጆቻቸቸው ጋር ሲጫወቱ” […]

“ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው፡፡” መዝ 59÷4

“ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው፡፡” መዝ 59÷4 ✞  እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ✞ እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው ፍጥረታት ሁሉ በአርአያውና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረው ፍጥረት ሰው ነው፡፡ ነገር ግን “ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ እንደ አላዋቂ ሆነ” ብሎ ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረው (መዝ 48 ÷12) ሰው ነጻነቱንና ታላቅነቱን ባለማወቁ ትዕዛዘ እግዚአብሔርን ጥሶ ሕጉን በማፍረሱ የሞት ሞት አገኘው፡፡ ኋላም እግዚአብሔር ሰውን ከሞት […]

“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፡፡” (መዝ 64÷11)

“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፡፡” (መዝ 64÷11) የዘመናት ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር ከዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ አሸጋግሮ እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ ከዓለም በፊት የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛ ዓለምንም አሳልፎ የሚኖር ዘመናትን የሚያመላልስ ደቂቃን በሰዓት፣ሰዓትን በዕለት፣ ዕለትን በወር፣ወርን በዓመት የሚጠቀልል ዓመታትንም የሚያቀዳጅ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ እርሱ ግን ለዘለዓለም የማይለወጥ መጀመሪያም መጨረሻም የሌለው አልፋና ዖሜጋ ራሱ […]

“ጻድቃን ወደ ጌታቸው ሄዱ እንጂ አልሞቱም” ቅዱስ ያሬድ

“ጻድቃንሰ ኢሞቱ ኀበ እግዚኦሙ ነገዱ”“ጻድቃን ወደ ጌታቸው ሄዱ እንጂ አልሞቱም” ቅዱስ ያሬድ በ መ/ር ሃፍታሙ ኣባዲ ከአባታቸው ጸጋ ዘአብ ከእናታቸው እግዚእ ኀረያ በስእለት የተወlዱት ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሕጻንነታቸው ጀምሮ ድንቅ ተአምራትን እያደረጉ ዕውቀትንና ኃይልን ተመልተው በመንፈስ ቅዱስ የጸኑ ቅዱስ አባት ናቸው። ዲቁና ይሾሙ ዘንድ ወደ ጳጳስ በተወሰዱ ጊዜ “ይህ ልጅ የተመረጠ ዕቃ ይሆናል” […]

“የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት”

“የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት” እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የትንሣኤና ዕርገት በዓል አደረሳችሁ፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሣ አራት ዓመት ነው፡፡ ያረፈችው ጥር 21 ቀን ነው፤ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በመደነቅ “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ፣ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኵሉ” (ድጓ ዘአስተርእዮ ማርያም) በማለት ስለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍት ገልጿል። ጥር 21 ቀን ጌታችን እልፍ አዕላፋት መላእክትን […]

የማኅበረ ቅዱሳን ካናዳ ማእከል 20ኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ።

የማኅበረ ቅዱሳን ካናዳ ማእከል 20ኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ። ማኀበረ ቅዱሳን ካናዳ ማእከል 20ኛ ዓመት የምሥረታ እና ጠቅላላ ጉባኤ መርሐ ግብር ከሐምሌ 26-28/2016 ዓ.ም በካልጋሪ አልበርታ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣የሀገረ ስብከቱ ጸሐፊና የደብረ ምሕረት መድኃኔ ዓለም ወቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪ መልአከ ሳህል ቀሲስ […]

ማኅበረ ቅዱሳን ካናዳ ማእከል የኦታዋ ንዑስ ማእከል በኪንግስተን ቅዱስ ሚናስ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ አካሄደ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምስራቅ ካናዳ ሀገረ ስብከት ስር የምትገኛው የደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በኪንግስተን ቅዱስ ሚናስ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ አካሄደ። በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተባባሪነት ከኢትዮጵያ የመጡት ቀሲስ ዶ/ር ደረጀን በተገኙበት በኪንግስተን የሚገኙ ምዕመናን ለማትጋትና በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲበረቱ ለማድረግ፤የኦታዋ ምዕመናንን በማስተባበር ጉዟቸውን ወደ ኪንግስተን በማድረግ በኪንግስተን ካሉ ምዕመናን ጋር በቅዱስ ሚናስ […]

ማስታወቂያ

ከበረከቱ በመካፈል የማኅበሩን አገልግሎት እንዲደግፉ ኃላፊነትዎን ይወጡ።

ሐዊረ ሕይወት

የፌስቡክ ልገሳ

የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን በየቤታችን ለማግኘት ምክንያት የሆነውን የማኅበራችንን ሚዲያ በመደገፍ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናበርክት::

ማኅበረ ቅዱሳን ካናዳ ማዕከል::