ሐዊረ ሕይወት
ማኅበረ ቅዱሳን ካናዳ ማእከል የቶሮንቶ ንኡስ ማእከል ከሳውዝ ዌስት ኦንታሪዮ ንኡስ ማእከል ጋር በመተባበር ወደ ሐሚልተን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር አከናወኑ።
የሕይወት ጉዞው የተከናወነው ለወላጆች፣ለወጣቶችና፣ለሕጻናት የተለያዩ መርሐ ግብራትን በማዘጋጀት ነው።
ለወላጆች የመዝሙር፣ የስብከተ ወንጌል፣የምክረ አበው መርሐ ግብራት የተከናወኑ ሲሆን።
ለወጣቶች መዝሙር፣ከኮፕቲክ(ግብፅ) ዲያቆናትን በመጋበዝ በእንግሊዝኛ የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብር፣ወጣቶች ለቤተ ክርስቲያን የልምድ ልውውጥ እንዲሁም የጥያቄና መልስ መርሐ ግብራት ተከናውነዋል።
ለሕጻናትም የቤተ ክርስቲያን መዝሙራት እንዲዘምሩ በማድረግና በሚረዱት መልክ የጥያቄና መልስ መርሐ ግብራትም ተከናውነዋል።
በሐዊረ ሕይወት ጉባኤው የማኅበረ ቅዱሳን አመሠራረት ከዝዋይ ስልጠና ጀምሮ እስከአሁን ስላለው አገልግሎት የልምድ ተሞክሮ መሥራች አባል በሆኑት በሊቀ ኅሩያን ቀሲስ አልዓዛር የቀረበ ሲሆን እንዲሁም በካናዳ ስላለው የማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት በንኡሳን ገለጻማእከላቱ ገለጻ ተደርጓል።



