ማኅበረ ቅዱሳን ካናዳ ማእከል የኦታዋ ንዑስ ማእከል በኪንግስተን ቅዱስ ሚናስ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ አካሄደ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምስራቅ ካናዳ ሀገረ ስብከት ስር የምትገኛው የደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በኪንግስተን ቅዱስ ሚናስ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ አካሄደ። በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተባባሪነት ከኢትዮጵያ የመጡት ቀሲስ ዶ/ር ደረጀን በተገኙበት በኪንግስተን የሚገኙ ምዕመናን ለማትጋትና በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲበረቱ ለማድረግ፤የኦታዋ ምዕመናንን በማስተባበር ጉዟቸውን ወደ ኪንግስተን በማድረግ በኪንግስተን ካሉ ምዕመናን ጋር በቅዱስ ሚናስ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉባኤያቸውን አካሂደዋል። በዕለቱም የቅዳሴ፣የትምህርተ ወንጌል፣የዝማሬና በአገልግሎት ዙሪያ የውይይት መርሐ ግብራት ተከናውነዋል።