በኤድመንተንና ካልጋሪ የሚገኙ ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ወጣቶች በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን መንፈሳዊ የጉዞ ጉባኤ አደረጉ።

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ያለፈው ቅዳሜ መስከረም 10
በካናዳ ማዕከል የተተኪ ትውልድ ክፍል እና የኤድመንተን እና ካልጋሪ ወጣት ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ኅብረት በጋራ ያዘጋጁት መንፈሳዊ ጉዞ እና ጉባኤ በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል።

ጉዞ የተደረገው ወደ ሬድ ዲር ሲሆን ጉባኤው በውዳሴ ማርያም: በጸሎተ ወንጌል /በጸሎተ ኪዳን/ ተጀምሯል።
በዋነኝነት የጉዞ ጉባኤው ለወጣቶች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማለትም በእንግሊዝኛ ቋንቋ መርሐ ግብራትን ለማከናወን ሲሆን ሲሆን በክርቲያናዊ የጾታ ግንኙነት እና ለትዳር ዝግጅት ማድረግ ምን መምሰል እንዳለበት በእንግሊዝኛ በአባታች ቀሲስ ሄርሞን ሰፊ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን ቀጥሎም ከትምህርቱ ጋር በተያያዙ ጥያቄዎች ዙሪያ ረዘም ያለ ጊዜ የወሰደ የቡድን ውይይት ተደርጓል::

የመርሐ ግብሩ ሙሉ ወጪ የተሸፈነው በማዕከሉ ሲሆን ስለማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎትም ገለጻ ተደርጓል፤ በጉባኤው ተሳታፊዎች ምግብ በማምጣት ተሳትፎ አድርገዋል። በአጠቃላይ ከ50በላይ የሚሆኑ እድሜያቸው ከ18ዓመት በላይ የሆኑ ወጣቶች ከሁለቱም ከተሞች ይህን ጉባኤ ተሳትፈዋል።