• እንኳን በደኅና መጡ !

ዘወረደ

“እኔ ነኝ በአንተ ልጠመቅ የሚገባኝ እንጂ አንተ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?” ማቴ. 3፥14-15

ቅዱስ ዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ አይሁዳውያንን ሲያጠምቅ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተራ ሰው መስሎ መጣ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ገርሞት “እኔ ነኝ በአንተ ልጠመቅ የሚገባኝ እንጂ አንተ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?” ማቴ. 3፥14-15 በማለት ማጥመቁን እምቢ አለ፡፡ ኢየሱስ ግን “አሁንስ ተው አትከልክለኝ የምጠይቅህን ጥምቀት ስጠኝ፡፡ ምክንያቱም ሕግን ሁሉ መፈጸም  ተገቢ ነው፡፡” ሲለው የጥምቀት ውኃ በራሱ አፈሰሰበት፡፡ ኢየሱስ ከተጠመቀ […]

“ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” ኢሳ 7÷14

++ ፈኑ እዴከ እምአርያምአድኅነኒ ወባልሐኒ እማይ ብዙኅወእምእዴሆሙ ለደቂቀ ነኪር መዝ ፻፵፫፥፯ ++ ትርጉም፦ እጅህን ከአርያም ላክከብዙ ውኃም አድነኝከባዕድ ልጆችም አድነኝ ምሥጢር፦ ረድኤትህን ከአርያም ላክ አንድም ልጅህን በሥጋ ላክ ከብዙ ጦር/ሠራዊት አድነኝ አንድም ከፍትወታት እኩያት ከኃጣውእ ርኩሳት ከፍዳ ከመከራ ነፍስ ፈጽመህ አድነኝ ከነናምሩድ ከነሳኦል ልጆች እጅ አድነኝ አንድም ከዲያብሎስ ወገኖች ሥልጣን አድነኝ:: እጅ/ክንድ ከአካል ሳይለይ የወደቀ […]

አዲስ ዓመት – ሐዲስ ሕይወት

ጳጉሜን ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱ ወቅቶችን ያፈራርቃል፤ ዝናብን ያዘንባል፤ ፀሐይን ያወጣል፡፡ ይህን ማድረጉ ለሰው ሁሉ ነው እንጂ በእርሱ ለሚያምኑ ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ሁሉ ግን ለሰው ሁሉ ከእግዚአብሔር የተሰጠ (የሚሰጥ) መክሊት ነው፡፡ የጊዜያዊውን ፀሐይ መውጣት፤ ዝናቡን መዝነብ ተመልክቶ ዘለዓለማዊ የምትሆን የጽድቅ ፀሐይ እንድትወጣለት፤ አምላካዊት የምትሆን የምሕረቱ ዝናብም በሕይወቱ እንድዘንምለት በእውነት የሚናፍቅና ወደ እግዚአብሔር […]

ፍሬውን ለመብላት ሥሩን ውሃ ማጠጣት

/ሊቀ ጠበብት ማኅቶት የሻው/ > ፍሬውን ለመብላት ሥሩን ውሃ ማጠጣት ይህ በምሳሌነት የቀረበ የአንድ ዕጽ /ዛፍ/ የእድገት ባህርይ ሲሆን ለሚሰጠው ፍሬና ጥቅም እውነተኛ አባባል ነው ። አንድ  ዛፍ አድጎ አንሰራፍቶ ጥሩ ፍሬ አፍርቶ ጥቅም ሊሰጥና ሊበላ የሚችለው ፣ ከምግብነት አልፎ በዛፍነቱም ለአዕዋፋት እና ለእንስሳት መጠለያ መከላከያ ሊሆን የሚችለው ቀጥ ብሎ አድጎ ሲፈለግ ለተለያየ አገልግሎትም እንዳደረጉት […]

ክብረ ክህነት

በክህነት አገልግሎት ውስጥ ሦስት ዋና ዋና ማዕረጋት አሉ። እነርሱም ጵጵስና፣ ቅስና እና ዲቁና ናቸው። የየራሳቸው ዋና ዋና የአገልግሎት ድርሻም አላቸው። ለምሳሌ፡- ጳጳሱ፡- አንብሮ እድ ላዕለ ጳጳስ ማለት ጳጳሳት ሲሾሙ እጁን በመጫን መሳተፍ፣ ቀሳውስትን መሾም፣ ዲያቆናትን መሾም፣ ማጥመቅና ቀድሶ ማቍረብ ናቸው። ቄሱ፡- ማጥመቅና ቀድሶ ማቍረብ ናቸው። ዲያቆኑ፡- መላላክ ነው። በማቴዎስ ወንጌል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ […]

Read more

‹‹እንደሚንሿሿ ጸናጽል ሆኛለሁ›› (፩ኛቆሮ.፲፫፥፩)

  ዲያቆን ዮሴፍ በቀለ  ጸናጽል ድምፁ መልካም የሆነ የምስጋና መሳርያ በመሆኑ ከቀደሙት ሌዋውያን አሁን እስካሉት የሐዲስ ኪዳን ቤተ መቅደስ መዘምራን ፣ ከቀደመው የሙሴ ድንኳን ዛሬ ቤተ ክርስቲያን ድረስ በእግዚአብሔር ፊት ይዘነው የምንቆመው መሳርያ ነው፡፡ ምስጋናችንም ሆነ መዝሙራችን ያለከበሮና ጸናጽል ምን ውበት ሊኖረው ይችላል ብለን እንጀምራለን? አንጀምረውም፡፡ የሊቃውንቱ መዳፍ ያለ ጸናጽል አይንቀሳቀስም፣ ቅኔ ማኅሌቱም ያለ ከበሮ […]

ስለምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? /ኢሳ. ፶፰፥፫/

በቀሲስ ስንታየሁ አባተ በኢሳያስ ዘመን የነበሩ እስራኤላውያን የተናገሩት ቃል ነው። እስራኤላውያን የሚጾሟቸው ብዙ አጽዋማት ነበሯቸው። ለምሳሌ ያህልም ብናይ በሳምንት ሁለት ጊዜ በሳምንት ሁለት ቀን ይጾሙ እንደነበር በሉቃ. ፲፰፥፲፪ ላይ ያለው ቃል ያስረዳል። ማክሰኞና ሐሙስ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ወደ ደብረ ሲና የወጣበትና ከዚያ የወረደበት ዕለት ለማሰብ እስራኤላውያን በሳምንት ሁለት ቀኖች ይጾሙ ነበር። በነቢዩ በዘካርያስ ትንቢትም ላይ […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria